የኢትዮጵያ የጽንስና የማህፀን ሐኪሞች ማህበር ደህንነቱ የተጠበቀ ጽንስ የማቋረጥ   ህክምናን መገደብ ሴቶችን እና ቤተሰቦችን ይጎዳል ብሎ ያሳስባል።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ አዋጅ ቁጥር 414/1997 (ግንቦት 1 ቀን 1997 ዓ.ም) የፅንስ ማቋረጥ ክፍል ከአንቀጾች 551-552 የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ለሚቃረኑ ጥረቶች ምላሽ ለመስጠት የኢትዮጵያ የጽንስና የማህፀን ሐኪሞች ማህበር የሚከተለውን የአቋም መግለጫ አውጥቷል።

ለአንድ ሰው መቼ ልጅ መውለድ እንዳለበትና ወላጅ መሆን እንዳለበት፣ እንዴት ማርገዝ እና ወውለድ አንደሚቻል እና ከስነተዋልዶ ጤና ጋር የተያያዙ ውሳኔዎች የተወሳሰበ እና ግላዊ ውሳኔን የሚፈልጉ ናችው። አመርቂ ውጤት ለማግኘት, ውስብስብ የሕክምና   ታሪክ   ላላቸው   ግለሰቦች እነዚህ ውሳኔዎች ብዙውን ጊዜ ከሕክምና ባለሙያዎች ጋር በትብብር መስራትን   ይጠይቃሉ። እርግዝና በታቀደ እና በሚፈለግበት ጊዜ እንኳን ህይወትን   ለማዳን   የፅንስ   ማቋረጥ   ሂደቶች መደረግ ያለባቸው ጊዜያት አሉ።

የኢትዮጵያ የጽንስና ማህፀን ሐኪሞች ማህበር አባላት ለሁሉም የተሻለ ጤና ለማስገኘት ቁርጠኞች ናቸው። ማህበሩ ፅንስ ማስወረድ በስሜታዊነት የሚነቀፍ ጉዳይ አለመሆኑን እና ከብዙ አቅጣጫ ማየት አንደሚያስፈልግ ይረዳል፡፡ የማህበሩ አባላት የታካሚዎቻቸውን   ደህንነት   ለመጠበቅ የተቻለውን ሁሉ የማድረግ ሃላፊነት ያለባቸው መሆኑን በመገንዘብ የሰነተዋልዶ ጤና ችግር ያለባቸውን ግለሰቦች ለመርዳት በትጋት ከሚሰሩት በመላው አገሪቱ ከሚገኙ አባላቱ ጋር ይቆማል፡፡ እርግዝና መቼ እንደሚቀጥል እና መቼ ይቋረጣል የሚሉት ውሳኔዎች የሕክምና ውሳኔዎች ሲሆኑ ከሕክምና ባለሙያዎች ጋር በመመካከር በግለሰብ ደረጃ መወሰድ አለባቸው።.

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የወንጀል ህግ አዋጅ ቁጥር 414/1997 (የግንቦት

1 ቀን 1997 ዓ.ም መመሪያ) ከአንቀጽ 551-552 የተመለከተው የፅንስ ማስወረድ ክፍል ድንጋጌዎች በተለይ በጤና እክል ምክንያት የተገለሉ እና ድሃ ለሆኑ ሴቶች የስነተዋልዶ ጤናን ለማሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል።

ይህ ህግ ከመፅደቁ በፊት በቀዶ ህክምና ፅንስ ለማስወረድ አስፈላጊውን ስልጠና የወሰዱ የሕክምና ባለሙያዎች ጥቂት ነበሩ፡፡ ለሕይወት አስጊ የሆነ የደም መፍሰስ፣   ኢንፌክሽን   ወይም   ጽንስ በማሀጸን ዉስጥ መሞት በሚያጋጥምበት ጊዜ ጽንሱን በፍጥነት ማቋረጥ የሚችል የጤና ባለሙያ በሌለባቸው ሁኔታዎችም ብዙ የሕክምና ክፍተቶች ነበሩ። ይህም የእናቶች ህመም እና ሞት ቁጥር በመላ ሀገሪቱ ወደ ከፍተኛ ደረጃ እንዲጨምር አድርጓል። ስለዚህም፣ ተመሳሳይ የስነተዋልዶ ጤና ችግሮች በመላ አገሪቱ ሲከሰቱ ማየት አንሻም፡፡ ለተሻለ የስነተዋልዶ ጤና   አጠባበቅ፣   የተሻለና ደህንነቱ የተጠበቀ የፅንስ ማቋረጥ አገልግሎትን ሁሌም እናበረታታለን።

የማህበራችን አባላት የታካሚን እንክብካቤን በፍጹም ወደጎን   የማይሉ   ቁርጠኞች   ናቸው፡፡ አባሎቻችን ከእርግዝና በፊት፣ በእርግዝና ወቅት እና ከእርግዝና በኋላ ታካሚዎቻቸውን ለመርዳት ያለመታከት መስራታቸውን በመቀጠል በመላ ሀገሪቱ ፍትሃዊ፣   በማስረጃ   ላይ   የተመሰረተ እንክብካቤ ለመስጠት እና ለመርዳት ዝግጁነታቸውን ያረጋግጣሉ። ሁሉም አባላት እያንዳንዱ ሰው የሚገባውን የህክምና እንክብካቤ ያለምንም ስጋት እንዲያገኝ ይሰራሉ። ፅንስ ማስወረድ አስፈላጊ የጤና እንክብካቤ ነው እና የስነተዋልዶ ጤና ነጻነት አስፈላጊ የሰው ልጅ መብት ነው። ፅንስ ማስወረድን ጨምሮ ስለሁሉም የጤና አጠባበቅ ውሳኔዎች የተሻለ የሚሆነው ግለሰቦች ከጤና ባለሙያዎችጋር አብረው ሲሰሩ ነው።

በ1997 የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ፅንስ ማስወረድ ከአንቀጽ 551-552 የተቀመጠውን የፅንስ ማስወረድ ድንጋጌዎች የመቃረን ጥረቶች የማይታሰብ ፣የግለሰቦችን ነፃነት እና የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ምልክቶች ናቸው እና ነፍሰጡር ሴቶች ላይ   የሚደርሰውን   የበሽታ   እና   ከፍተኛ   የሞት መጠን ለማባባስ አደገኛ እርምጃ ነው። እ.ኤ.አ. በ1997 የወጣው የወንጀለኛ መቅጫ ህግ (ግንቦት 1 ቀን 1997 የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መመሪያ) ፅንስ ማስወረድ እንክብካቤን በዋናነት ተጠቃሚ ያደረጋቸው አብዛኞቹ የተገለሉ እና በጤና አገልግሎት ኢፍትሃዊነት እየተሰቃዩ ያሉ ድሃ ሴቶችን ነው።

የኢትዮጵያ የጽንስና የማህፀን ሐኪሞች ማህበር በ1997 የወንጀለኛ መቅጫ ህግ (ግንቦት 1 ቀን 1997 የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መመሪያ) በውርጃ እንክብካቤ አቅርቦት ላይ የተደነገገዉን የፅንስ ማቋረጥ እንክብካቤን ጨምሮ ሁሉም ሴቶች ሙሉ የስነተዋልዶ   ጤና   አገልግሎት   የማግኘት መብትን ይደግፋል። የኢትዮጵያየ ጽንስና የማህፀን ሐኪሞች ማህበር ፖሊሲ አውጪዎች ደህንነቱ የተጠበቀ እና አስፈላጊ የውርጃ እንክብካቤ ተደራሽነትን እንዲጠብቁ ያበረታታል፡፡ የተሻለና ፍትሃዊ የሆነ   የፅንስ   ማቋረጥ   አገልግሎት    በቀላሉ    ማግኘት    እንዲቻልም    መምከሩን    ይቀጥላል። በ1984 ዓ/ም የተመሰረተው የኢትዮጵያ የጽንስና የማህፀን ሐኪሞች ማህበር   የህክምና ባለሙያዎች ማህበር ነው። የኢትዮጵያ የጽንስና የማህፀን ሐኪሞች ማህበር ሴቶችን፣ ልጃገረዶችን እና ጥንዶችን የተለያዩ የስነተዋልዶ ጤና ችግሮችን የሚንከባከቡ እና ትምህርት የሚሰጡ፣ ጥናትና ምርምርን የሚያካሂዱ እና የአባላትን አገልግሎት ለሚሹ ሰዎች ሁሉ ጥሩ እና ፍትሃዊ የሆነ የስነተዋልዶ ጤና ውጤቶችን ለማስፋት በደጋፊነት የሚሳተፉ ከ820 በላይ አባላትን ይወክላል።

ለበለጠ መረጃ የኢትዮጵያ የጽንስና የማህፀን ሐኪሞች ማህበር ድህረገጽን ይጎብኙ (www.esog- eth.org)